የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት (Ph.D. Week in Data Science) በኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ነው
የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት (Ph.D. Week in Data Science) በኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ነው
********************************************
የጎንደር ዩኒቨርሰቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ከኢንፎርሜሽን ሳይንስ ት/ክፍል ጋር በመተባበር የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት (Ph.D. Week in Data Science) በአጼ ተዎድሮስ ግቢ ድህረ ምረቃ አዳራሽ ዛሬ ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም እያካሄደ ይገኛል፡፡
የዩኒቨርሲቲያችን አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ ዶ/ር አገኘሁ ተስፋ፣ የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ይልቃል ሙሉአለም፣ የቤተ-መጽሃፍት እና ዶክመንቴሽን ዳይሬክትር አቶ ብርቁ ገድፍ፣ በኮሌጁ የሚገኙ ተመራማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የድህረ- ምረቃ ተማሪዎች በፕሮግራሙ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ይልቃል ሙሉአለም በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት እንደተጀመረ እና የዳታ ሳይንስ ፒ.ኤች.ዲ ተማሪዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ኮርስ ጨርሰው የመመረቂያ ፕሮፖዛላቸውን ለውስጥ ገምጋሜዎች የሚያቀርቡበት መድረክ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም አሁን ላይ በኮሌጁ 7 የፍልስፍና ዲግሪ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በቀጣይ በሶስቱም የፍልስፍና ዲግሪ ፕሮግራሞች ማለትም በዳታ ሳይንስ፣ በዲጅታል ትራንስፎርሚሽን እና ኢኖቬሽን እንዲሁም በሳይበር ደህንነት አዳዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ተናግረዋል፡፡
እንዲህ አይነት የምርምር መድረኮች መካሔዳቸው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና በድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ላይ የሚታየውን ለውጥ ለማወቅ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርጉ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ተናግረዋል፡፡ የፒ.ኤች.ዲ ሴሚናር መካሔዱ ከነባር ምሁራን ልምድ የመማር እድልን እንደሚፈጥር እና ሁሉም የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችና የኮሌጁ መምህራኖችም ሆኑ ሌሎች ዝምድና ያላቸው ከሌሎች ኮሌጅ መምህራኖችን በመጋበዝ በፕሮግራሙ መሳተፍ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። አያይዘውም የፒ.ኤች.ዲ ሴሚናር በኮሌጁ በተደጋጋሚ መደረግ እንዳለበት እና በኮሌጁ ስር የሚገኙ ከፍተኛ ተመራማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ተማሪዎቻችን ልምድ ካላቸው መምህራን እርስ በእርስ የሚማሩበት ሳምንት መሆኑን አስገንዝበዋል።
********************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም
What's Your Reaction?