የጎንደር ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት የሁለትዮሽ የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

*********************************************
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የሁለትዮሽ የጋራ ስምምነት ሰነድ  ዛሬ የካቲት 3/2018ዓ.ም በፕሬዚዳንት ህንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረመ፡፡

በዚህ መርሀ- ግብር የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት አፀደወይን፣ የዩኒቨርሲቲያችን ም/ፕሬዚዳንቶች፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ፣ የኢንስቲቲዩቱ ዳይሬክተሮች፣ የዩኒቨርሲቲያችን የኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ዶ/ር ወርቁ አበበና ሌሎች ዲኖች፣ ፕሮፌሰሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት አፀደወይን በመርሀ -ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣  እንደ ሀገር የዘርፉን አቅም አስቀድሞ በመረዳት የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት በማቋቋም እየተሰራ ያለውን ተምሳሌታዊ ስራና ለቴክኖሎጂው የተሰጠውን ትልቅ ትኩረት በተግባር ውጤት እያሳየ በመሆኑ መንግስትንና ኢንስቲቲዩቱን በራሳቸው በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም አመስግነዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ይህንን ሀገራዊ ራዕይና የቴክኖሎጂ ሽግግር በላቀ ደረጃ መደገፍ እንዲችል በሰው ሀይል ልማት ረገድ ትልቅ እምርታ የሚያስመዘግቡ አዳዲስ የድህረ- ምረቃ ፕሮግራሞችን ለመክፈት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ የተፈረመው የሁለትዮሽ የመግባቢያ ሰነድም ይህን ዕድል ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር የሚጠቀሙበት ዋነኛ መሳሪያ እንደሆነና ፊርማው ወረቀት ላይ የሚቀር ሳይሆን ለሀገራችን ችግሮች የጋራ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መፍትሄዎች የሚፈልቁበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ መድረኩ እንዲዘጋጅ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን የኢንፎማቲክስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ወርቁ አበበን፣ የኢንስቲቲዩቱ ከፍተኛ አመራሮችንና  ተሳታፊዎችን አመስግነዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ  በበኩላቸው መርሀ-ግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ያስጀመሩ ሲሆን፣ እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሰው ሰራሽ አስተውህሎትን በአግባቡ ለመጠቀምና ለማህበረሰቡ በሚጠቅም መልኩ ቴክኖሎጂውን እንዴት መጠቀም እንደሚገባ አፅንዖት ተሰጥቶበት ውይይት ሊደረግ እንደሚገባ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡

በዕለቱ የተፈረመው የጋራ የመግባቢያ ሰነድ የተቋሙን ትኩረት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በማጣመር በህብረተሰቡ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚያስችል ያላቸውን እምነት ባደረጉት ቁልፍ ንግግር የገለፁት የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል 2030 ራዕይ እየተጓዘችበት በሚገኘው በዚህ ወቅት መሰል ትብብሮች በጣም እንደሚያስፈልጉ ገልፀዋል፡፡ ስምምነቱ የዲጂታል ስርዓት ትግበራ ዕውን ለማድረግ በጋራ መስራት ላይ ያለመ እንደሆነና ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን በስነ- ምህዳራዊ መልኩ ማልማት፣ ብቁ የሰው ሀይል አቅም የመገንባትና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተማሪዎች የሚመሩ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አቶ ይታገሱ ደሳለኝ አክለው ተናግረዋል። ወደፊትም በተለያዩ መንገድ  ከኢንስቲቲዩቱ ጋር በቅርበት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበው መድረኩን ያመቻቹ አካላትን አመስግነዋል፡፡

በመቀጠልም በኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የምርምር አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ሰለሞን ዘውዴ በኩል "AI for social Goods research center" ማቋቋም ላይ መሰረት ያደረገ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን፣ በተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ለተጠየቁት ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸው በዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት በዶ/ር አሥራት አጸደወይን የመዝጊያ ንግግር መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡

በቀጣይ በዚህ ዙሪያ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ከማዘጋጀት ጋር ተያይዞ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣  ከዚህ መርሀ- ግብር ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው አዳሪ ት/ቤት፣ በማህበረሰብ ት/ቤቱና በፋሲለደስ ት/ቤት የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ክለብ መቋቋሙን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ 
**********************
ለልህቀት እንተጋለን!

የካቲት 3/2018 ዓ.ም

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow