የኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት እያካሄደ ነው

የኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት እያካሄደ ነው
የኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት እያካሄደ ነው
*********************************************
በጎንደር ዩኒቨርሰቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ስር የሚገኘው የኢንፎርሜሽን ሳይንስ ት/ክፍል የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት ከጥር 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ ድህረ - ምረቃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ወርቁ አበበ፣ በኮሌጁ የሚገኙ ልምድ ያላቸው አንጋፋና ጀማሪ መምህራን እንዲሁም ተመራማሪዎች በፕሮግራሙ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በመርሀ-ግብሩ በኮሌጁ ያሉ ክፍተኛ ተመራማሪዎችና መምህራን ከጀማሪ ተመራማሪዎችና መምህራን (Graduate assistants)ጋር እርስ በእርስ የሚማሩበት ሳምንት እንደሚሆን ዶ/ር ወርቁ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ተናግረዋል፡፡
አሁን አሁን የፒ.ኤች.ዲ ሳምንት ማካሄድ በዩኒቨርሲቲው በሁሉም ኮሌጆች እንደ ባህል እየተወሰደ መምጣቱ እንዳስደሰታቸው የገለጹት ዶ/ር ካሳሁን፣ መሰል መርሀ- ግብሮች መካሄዳቸው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ አይነተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን በአካዳሚያዊ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
*************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥር 01/2018 ዓ.ም

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow